1.2 KiB
1.2 KiB
የሰነፍ ምኞት ራሱን ይገድለዋል
ጸሐፊው ሰውየው ስለሚፈልገው ነገር ሲናገር ምኞቱ ሰነፍ ሰው ሊገድል የሚችል ሰው አድርጎ ገልጾታል፡፡ እዚህ ላይ ሰነፍ ሰው ስራ ፈት እና የማይሰራ መሆን ይፈልጋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰነፍ ሰው ስራ መፍታት ይወዳል ከዚህ የተነሳ ይሞታል” ወይም “ሰነፍ ሰው ሊሰራ ካለመፈለጉ የተነሳ ይሞታል” (ሰውኛ ዘይቤ እና የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ) )
እጆቹ አይፈቅዱም
እጅ ለሰውየው ተዛምዶአዊ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አይፈቅድም” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)
ይመኛል
በብርቱ ይፈልገዋል
ይሰጣል፤ አይሰስትም
“አይሰስትም” የሚለው ቃል በአዎንታዊ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፤ የሚሰጠው ነገር ደግሞ በግልጽ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሊሰጥ የሚገባውን ሁሉ ይሰጣል” ወይም “በቸርነት ይሰጣል “ (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)