am_tn/pro/21/11.md

1.6 KiB

ፌዘኛ ሲቀጣ

ይህ በገቢር ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው ፌዘኛውን ሲቀጣ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

አላዋቂ

“ልምድ የሌላቸው” ወይም “ብስለት የሌላቸው”

ፈዘኛ

“በሌሎች ላይ የሚያፌዝ”

ጥበበኛ ሰው ሲገሰጽ

ይህ በገቢር ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው ጥበበኛውን ሰው ሲገስጸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እውቀትን ይጨምራል

እዚህ ላይ እውቀት አንድ ሰው ሊጨብጠውና ለራሱ ሊወስደው የሚችለው እቃ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጽድቅን የሚያደርግ ሰው

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ማንኛውም ጻድቅ ሰው ወይም 2) “ጻድቅ የሆነው እግዚአብሔር”

ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል

“ለቤት ጥንቃቄ የተሞላበት ትኩረት ያደርጋል” “ቤቱ ላይ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማየት ይጠብቃል”

እርሱ ክፉውን ወደ ጥፋት ያወርደዋል

እዚህ ላይ ጥፋት አንድ ሰው የሚወሰድበት ቦታ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ያጠፋቸዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)