am_tn/pro/21/09.md

2.2 KiB

በጣራ ማእዘን

በዚያን ጊዜ የነበሩ ቤቶች ለጥ ያለ ጣራ ነበራቸው፡፡ የጥንት እስራኤላውያን ጣራቸውን ለመስራት ብዙ ጊዜ ይወስድባቸው ነበር፡፡ ጣራው ከቤቱ ውስጠኛው ክፍል ይልቅ ቀዝቃዛ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ለመኝታ የሚሆን ትልቅ መጠለያ በጣራው በአንዱ ማእዘን ላይ ይሰሩ ነበር፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ጠበኛ ሚስት

“ብዙ ጊዜ የምትጨቃጨቅና የምታማርር ሚስት”

የክፉ ሰው ምኞት ክፋትን አጥብቆ ይመኛል

ጸሐፊው ስለ ሰው ምኞት ማለትም ለሚበላና ለሚጠጣ ነገር ስላለው ፍላጎት ሲናገር አንድን ነገር እንደሚፈልግ ሰው አድርጎ ገልጾታል፡፡ “ክፉ” የሚለው ቃል ክፉ ሰዎችን የሚያመለክት የስም ቅጽል ሲሆን “ክፋት” የሚለው ቃል ደግሞ ክፉ ድርጊቶችን የሚወክል የስም ቅጽል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎች ለመብላትና ለመጠጣት እንደሚመኙ እንደዚሁ ክፉ ድርጊቶችን ለመፈጸም ይመኛሉ” (ሰውኛ ዘይቤ እና የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)

መመኘት

አጥብቆ መፈለግ

ጎረቤቱም በዓይኖቹ ውስጥ ምንም ደግነት አያይም

“ደግነት መፈለግ” የሚለው ፈሊጥ አንድ ሰው ደግነት ለሚፈልገው ሰው ማረጋገጫ ሲሰጠውና በደግነት ሲያደርግለት ማለት ነው፡፡ በተጨማሪ ዓይኖች ማየትን ይወክላል፣ ማየት ደበደግነት ግሞ ሰውየው ለሌሎች ሰዎች ያለውን ሃሳብና አመለካከት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጎረቤቱ ከእርሱ ምንም ዓይነት ደግነት አላገኘም” ወይም “ለጎረቤቱ ደግትን አላሳየም” (ፈሊጥ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)