1.4 KiB
1.4 KiB
ትጉ ሰው
ይህ የስም ቅጽል እንደ ስም ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትጉ ሰው” ወይም “ጠንክሮ የሚሰራ ሰው” (የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)
ወደ ድህነት ይመጣል
“ድህነት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ድሃ ይሆናል” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
ሃብትን ማግኘት
“ሃብትን ማከማቸት”
ውሸታም ምላስ
ምላስ አንደበቱ ይናገር ዘንድ ሰው ለሚጠቀምባቸው ቃላቶች ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ውሸት መናገር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
የሚጠፋ ተን
ጸሐፊው ሰው በውሸት የሚያገኘውን ሃብት በማለዳ በፍጥነት ከሚጠፋ ተን ጋር አመሳስሎታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚጠፋ ተን” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
የሚገድል ወጥመድ
ጸሐፊው ሰው በውሸት የሚያገኘውን ሃብት በአዳኝ ወጥመድ ላይ እንደሚደረገው የማታለያ ምግብ እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)