am_tn/pro/21/03.md

1.9 KiB

ቅን የሆነውን ነገር ማድረግ

“እግዚአብሔር ትክክል እንደሆነ የሚያስበውን ነገር ማድረግ”

ፍትህን … ማድረግ

“እግዚአብሔር ሰዎች ሌሎች ሰዎችን ሊይዙ የሚፈልገውን ዓይነት አያያዝ ለሰዎች ማድረግ”

ለእግዚአብሔር ፍትህ የበለጠ ተቀባይነት አለው

“ፍትህ - እግዚአብሔር ይህን የበለጠ ይፈልገዋል”

ትቢተኛ ዓይንና ኩሩ ልብ

“ዓይን” እና “ልብ” የሚሉት ቃላት ራሱን ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እንደሚሻል ለሚቆጥርና ሌሎች ሰዎች ይህን ሃሳቡን እንዲያወቁለት ለሚፈልግ ሰው ተዛምዶአዊ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እንደሚሻሉ ሰዎች እንዲያስቡ የሚፈልጉ ሰዎች” (ተዛምዶአዊ እና ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ትዕቢተኛ ዓይን

ይህ እርሱ ከእነርሱ ይልቅ እንደሚሻል እንደሚያስብ ሌሎች ሰዎች እንዲያውቁለት ለሚፈልግ ሰው ተዛምዶአዊ ዘይቤ ነው፡፡ (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ኩሩ ልብ

ይህ እርሱ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ የተሸለ እንደሆነ ለሚያስብ ሰው ተዛምዶአዊ ዘይቤ ነው፡፡ (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

የክፉ ሰውም መብራት

ክፉ ሰውን የሚያግዙ ነገሮች በሙሉ እንደ መብራት እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰውን እንደ መብራት የሚያግዙ ነገሮች በጨለማ እንዲያይ ይረዱታል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)