am_tn/pro/19/23.md

2.1 KiB

እግዚአብሔርን ማክበር ሰዎችን ወደ ሕይወት ይመራል፤ እንዲህ ያለውም ሰው ይረካል

ይህ ሰዎች እግዚአብሔርን ቢያከብሩ ረጅም እድሜ ይኖራሉ ማለት ነው፡፡ የዚህ ዓረፍተ-ሃሳብ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔርን የሚያከብሩ ሰዎች ረጅም እድሜ ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርን የሚያከብር ማንኛውም ሰው ይረካል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ያለው ሰው

እዚህ ላይ “ያለው” የሚለው ቃል የሚያመለክተው “እግዚአብሔርን ማክበር” ነው፡፡

ይረካል በመከራም አይጎዳም

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይረካል፤ ምንም ነገር አይጎዳውም” ወይም “ይረካል፤ በደህንነት ይጠበቃል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰነፍ

ይህንን በምሳሌ 10፡26 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡

እጁን በሳህን ውስጥ ያጠልቃል

“እጁን በሳህን ውስጥ ያስገባል” ወይም “እጁን በራሱ ሳህን ውስጥ ያስቀምጣል፡፡” በዘመናችን በብዙ ባህሎች ውስጥ እንደሚሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ባህል ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚበሉት በእጃቸው ነበር፡፡

ወደ አፉም እንኳ እንደገና መልሶ አያመጣውም

እጁን እንደገና ወደ አፉ መልሶ አያመጣውም ምክንያቱም እጅግ በጣም ሰነፍ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን በጣም ሰነፍ ከመሆኑ የተነሳ ራሱን ለመመገብ እጁን መልሶ ወደ አፉ ማምጣት አይችልም፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)