am_tn/pro/19/19.md

2.2 KiB

ንዴቱን መቆጣጠር የማይችል ሰው

ይህ ፈሊጥ ሲሆን በቀላሉ የሚበሳጭ ሰውን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ሰው” ወይም “በቶሎ የሚቆጣ ሰው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ቅጣቱን ማግኘት አለበት

ይህ የሚያመለክተው እርሱ ሲቆጣ የሚከተለውን አሉታዊ ውጤት የተሸከመውን ሰው ነው፡፡ የዚህ ዓረፍተ-ሃሳብ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የቁጣውን አሉታዊ ውጤት መሸከም አለበት” ወይም “በቁጣው የፈጸመው ድርጊት አሉታዊ ውጤት መሸከም አለበት” (ፈሊጥ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ብታድነው

“ብትታደገው፡፡” ይህ የሚያመለክተው ከቁጣው የተነሳ ከሚወስደው እርምጃ እርሱ ማዳን ነው፡፡ የዚህ ዓረፍተ-ሃሳብ ትርጉም በቀላሉ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በቁጣ ከተሞላ በኋላ ብታድነው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለሁለተኛ ጊዜ

“ሌላ ጊዜ” ወይም “እንደገና” (ደረጃ የሚያሳይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)

ምክርን ስማ ተግሳጽንም ተቀበል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ናቸው፣ የተደጋገሙት ነገሩ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

ምክርን ስማ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ እዚህ ላይ “ስማ” የሚለው እንዲያው ዝም ብሎ በጆሮ መስማት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ከተሰጠህ ምክር መማርና ምክሩን መከተል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለምክር ትኩረት ስጥ” ወይም “ምክርን ተከተል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)