am_tn/pro/19/17.md

2.0 KiB

ለድሃ ቸር የሆነ ሰው ለእግዚአብሔር ያበድራል

እግዚአብሔር ለድሃ የተደረገውን ቸርነት ለእርሱ እንደተደረገ ይቆጥራል፡፡ ሰዎች ለድሃ ደግነትን የሚገልጡበት አንዱ መንገድ በመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለድሃ የሚሰጥ ሰው ለእግዚአብሔር ይሰጣል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ድሃ

ይህ ድሃ ሰዎችን የሚያመለክት ነወ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ድሃ የሆኑ ሰዎች” ወይም “ድሃ ሰዎች” (የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)

ተስፋ ሳለ

ይህ የሚያመለክተው ልጅ ገና በሕጻንነቱ ሳለና ቅጣትና ተግሳጽ ሊቀበል የሚችልበትን ጊዜ ነው፡፡ የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ገና ልጅ ሳለ” ወይም “ሊማር በሚችልበት ጊዜ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሞቱንም እየተመኘህ ዝም ብለህ አትየው

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ይህ ሀረግ የሚገልጸው ልጅህን መቅጣት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን ልጅህ እንዳይሞት አስከፊ በሆነ ሁኔታ አትቅጣው” ወይም 2) ይህ ሀረግ የሚገልጸው ልጅህን ባትቀጣው ምን ሊሆን እንሚችል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ካልቀጣኸው ራሱን እንዲያጠፋ እያገዝኸው ነው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እየተመኘህ ዝም ብለህ አትየው

ይህ ፈሊጥ ሲሆን ትርጉሙም አንድ ነገር እንዲከናወን መጨከን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱን ዝም ብሎ ማየት” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)