am_tn/pro/19/13.md

1.4 KiB

ለአባቱ መጥፊያ ነው

“አባቱን ያጠፋዋል”

ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ የውኃ ነጠብጣብ ናት

ይህ የሚናገረው ስለ ጨቅጫቃ ሚስት ሲሆን እርሷ የማታቋርጥ የውኃ ነጠብጣብ እንደሆነች አድርጎ ገልጿታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጨቅጫቃ ሚስት እንደማያቋርጥ የውኃ ነጠብጣብ ነዝናዛና በጥባጭ ናት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጨቅጫቃ ሚስት

“ተከራካሪ ሚስት” ወይም “ስምምነት የሌላት ሚስት”

ቤትና ሐብት ከወላጆች ይወረሳል

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ልጆች ቤትና ሐብት ከወላጆች ይወርሳሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

አስተዋይ

ይህን ቃል በምሳሌ 12:23 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡

አስተዋይ ሚስት ከእግዚአብሔር ናት

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር አስተዋይ ሚስት ይሰጣል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)