1.4 KiB
1.4 KiB
ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም
ይህ በአዎንታዊና በገቢር ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ ይህንን በምሳሌ 19:5 እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ሐሰተኛ ምስክርን በእርግጠኝነት ይቀጡታል” (ጥምር አሉታ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
ውሸት ያሰራጫል
ይህ ዘይቤአዊ ንግግር “ያሰራጫል” የሚለውን ቃል ሳያቋርጡ መዋሸትን ለማመልከት ተጠቅሞበታል፡፡ ይህንን በምሳሌ 6:19 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ያለማቋረጥ ይዋሻል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)
አይገባውም
“ትክክል አይደለም”
ቅንጦት
የባለጠግነትና የደስታ ሁኔታ
ለባርያ ደግሞ የከፋ ነው
“ይህ” እና “አይገባውም” የሚሉት ቃላት ከቀደመው ሀረግ ግልጽ ተደርገዋል፡፡ ሊደገሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለባርያ ፈጽሞ አይገባውም” ወይም “ለባርያ ከዚህም የከፋ ነው” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)