1.4 KiB
1.4 KiB
ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይታለፍም
ይህ በአዎንታዊና በገቢር ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ሐሰተኛ ምስክርን በእርግጠኝነት ይቀጡታል” (ጥምር አሉታ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
ውሸትንም የሚያሰራጭ ሰው አያመልጥም
እርሱ ይያዛል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ውሸት የሚያሰራጨውን ሰው ይይዙታል” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)
ውሸት ያሰራጫል
ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ እዚህ ላይ “ያሰራጫል” የሚለው ቃል የማያቋርጥ ውሸትን ያመለክታል፡፡ ይህንን በምሳሌ 6:19 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ያለማቋረጥ ይዋሻል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)
ቸር ሰው
ብዙ ጊዜ አንዳንድ ነገሮችን ለሰው የሚሰጥ
ሁሉ ጓደኛ ይሆነዋል
“ሁሉ” የሚለው ቃል ግነት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁሉ ጓደኛው የሆነ ይመስላል” ወይም “ሁሉም ሰው ጓደኛው ነው ማለት እንችላለን” (ግነትና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)