am_tn/pro/19/03.md

1.1 KiB

ልቡም ይቆጣል

እዚህ ላይ ስሜቱን አጽንዖት ለመስጠት ሲባል ሰው “በልቡ” ተወክሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይቆጣል” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ሐብት ብዙ ጓደኞችን ይጨምራል

ይህ ሀብታም ሰው ብዙ ጓደኞች ይኖረዋል ምክንያቱም ሀብት ሰውን ይስባል ማለት ነው፡፡ የዚህ ሃሳብ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሀብታም ሰዎች በቀላሉ ብዙ ጓደኞች ያገኛሉ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ

ድሃ ሰው ግን ከወዳጆቹ የተለየ ነው

ድሃ ሰው በድህነቱ ምክንያት ከብዙ ጓደኞቹ ይለያል፡፡ የዚህ ሃሳብ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ድህነት ሰው ጓደኞቹን እንዲያጣ ያደርጋል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)