am_tn/pro/19/01.md

1.8 KiB

ድሃ ሰው ይሻላል

“ድሃ ሰው መሆን ይሻላል”

በሃቀኝነት የሚራመድ ሰው

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ እዚህ ላይ መራመድ መኖርን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሐቀኝነቱ የሚኖር ሰው” ወይም “እውነተኛ ሕይወት የሚኖር ሰው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

በንግግሩ ጠማማ ነው

“ንግግር” የሚለው ቃል እንደ ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጠማማነት ይናገራል” ወይም “በክፉ መንገድ ይናገራል” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ያለ እውቀት አንድን ነገር መመኘት

ይህ የሚያመለክተው አንድን ነገር በትክክለኛ መንገድ እንዴት መስራት እንዳለባቸው እውቀት ሳይኖራቸው ለመስራት የሚሞክሩ ሰዎችን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የምትሰራው ነገር ምን እንደሆነ ሳታውቅ በትጋት መስራት” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ

በችኮላ የሚሮጥም መንገዱን ይስታል

ይህ የሚናገረው ነገሮችን በጣም በችኮላ ስለሚሰራና ስህተትን ስለሚፈጽም ሰው ሲሆን ይህን ሰው በችኮላ እንደሚሮጥና መንገዱን እንደሚስት ሰው አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም በችኮላ የሚሰራ ሰው ስህተት ይፈጽማል” ወይም “በጣም በችኮላ የሚሰራ ሰው የተሳሳተ ምርጫ ያደርጋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)