am_tn/pro/18/19.md

2.9 KiB

የተበደለ ወንድምን መርታት ጠንካራ ከተማን ከማሸነፍ ይልቅ በጣም የከበደ ነው

ይህ ጠንካራ ከተማን በጦርነት ማሸነፍ በጣም አስቸጋሪ ከመሆኑ ጋር በማነጻጸር ከበደልከው ወንድምህ ጋር ሰላም መፍጠር በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወንድምህን ከበደልከው እንደገና ከእርሱ ጋር ሰላምን ለመፍጠር መንገድ መፈለግ ከተማን ለማሸነፍ ጦርነት ከመግጠም በላይ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጠብ እንደ ግንብ ብረት ነው

ይህ የሚናገረው የግንብ ብረት መስበር በጣም አስቸጋረ ከመሆኑ ጋር በማነጻጸር ለጠብ መፍትሔ መስጠትም አስቸጋሪ መሆኑን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠብን ማስቆም የግንብ ብረትን እንደመስበር በጣም አስቸጋሪ ነው” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ግንብ

የተመሸገ ስፍራ

የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል፤ ከንፈሩም ከሚያፈራው ይጠግባል

ሁለቱ መስመሮች አንድ ዓይነት ትርጉም አላቸው፤ ጥቅም ላይ የዋሉት ደግሞ ለተነገረው ነገር አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ሁለቱን በአንድ ላይ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰው የሚናገረው መልካም ነገር ባመጣው ውጤት ይረካል” (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

የአፉ ፍሬ

ይህ ሰው ስለሚናገረው መልካም ነገሮች የሚናገር ሲሆን ከአፉ የሚወጣ ፍሬ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበብ የተሞላ ንግግሩ” ወይም “መልካም ቃላቶቹ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሆዱ ይሞላል

ይህ በተናገሩት ነገር ምክንያት በመጣው ውጤት ስለጠገቡ ወይም ስለረኩ ሰዎች የሚናገር ሲሆን እንደበሉና እንደጠገቡ አድርጉ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ረክቷል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የከንፈሮቹ ምርት

ይህ ሰው ስለሚናገረው መልካም ነገር የሚናገር ሲሆን ከዛፉ ላይ እንደሚሰበሰብ ፍሬ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእርሱ ጥበብ የተሞላ ንግግር” ወይም “የእርሱ መልካም ቃላት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ይረካል

“እርሱ ይደሰታል”