am_tn/pro/18/17.md

1016 B

ጉዳዩን ለማሰማት የመጀመርያ ነው

ይህ ተቀናቃኙ ቀርቦ ጉዳዩን ከማሰማቱ በፊት ቀድሞ ጉዳዩን የሚያሰማውን ሰው የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጉዳዩን ለማሰማት የመጀመርያው ሰው” ወይም “ጉዳዩን ያሰማ የመጀመርያው ሰው” (ደረጃ የሚያሳይ እና የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)

እጣውን ማውጣት

“እጣ ማውጣት”

ሃይለኛ ጠላቶችንም ትለያለች

ይህ በክርክር ምክንያት ክፉኛ የሚጣሉ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ ሲለያዩ በክርክራቸው ምክንያት መጣላታቸውን ያቆማሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ተቀናቃኞች በክርክራቸው ምክንያት መጣላታቸውን እንዲያቆሙ ያደርጋል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)