am_tn/pro/18/11.md

2.2 KiB

የባለጸጋ ሐብት የእርሱ የተመሸገ ከተማ ነው

ይህ በብልጽግናው ስለሚታመን ሀብታም ሰው የሚናገር ሲሆን ሀብቱ እርሱን የሚጠብቀው የተመሸገ ግንብ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጿል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከተማ በተመሸገ ግንብ ላይ እንደሚደገፍ ሁሉ ባለጸጋ ሰው ደግሞ በሀብቱ ላይ ይደገፋል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ባለጸጋ

ይሀህ ሀብታም ሰዎችን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሀብታም ሰው” (የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)

የተመሸገ ከተማ

በግድግዳና በግንብ የተከበበች ጠንካራ ከለላ ያላት ከተማ

ሃሳቡም እንደ ረዥም ግንብ ነው

ይህ የሚናገረው ከፍ ያለ ግንብ በከተማ ውስጥ ያሉትን በደህንነት እንዲጠበቁ እንደሚያደርግ ሁሉ ሀብቱ በደህንነት ይጠብቀኛል ብሎ ስለሚያምን ባለጸጋ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከፍ እንዳለ ግንብ ሀብቱ ይጠብቀኛል ብሎ ያስባል” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከውድቀቱ በፊት የሰው ልብ ትዕቢተኛ ይሆናል

“በመጀመርያ የሰው ልብ በትዕቢት ይሞላል፣ ነገር ግን ወዲያውኑ ውድቀቱ ይመጣል”

ውድቀት

ይህ በሰው መልካም ስምና ጤንነት ላይ የሚመጣውን ውድቀት የሚያመለክት ነው፡፡

የሰው ልብ

እዚህ ላይ ለሃሳቡና ለስሜቱ አጽንዖት ለመስጠት ሰው በልቡ ተtወክሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰው” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ትህትና ግን ክብርን ቀድሞ ይመጣል

“ትህትና” የሚለው ቃል እንደ ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፣ “ክብር” የሚለው ደግሞ እንደ ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰው ከመከበሩ በፊት ትሁት ሊሆን ይገባዋል” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)