1.3 KiB
1.3 KiB
ጽድቅን ለሚያደርጉ … መልካም አይደለም
እነዚህ ሀረጎች በአዎንታዊ ቅርጽ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለክፉ ሰው የሚገባውን ዋጋ መክፈል፣ ለጻድቃን ደግሞ ፍትሃዊ መሆን መልካም ነው (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)
የሞኝ ከንፈሮች ያመጣሉ
እዚህ ላይ ንግግሩ ላይ አጽንዖት ለመስጠት ሲባል ሞኝ “በከንፈሮቹ” ተወክሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሞኝ የተናገረው ያመጣል” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)
ያመጣል
“ምክንያት ይሆናል”
አፉም በትርን ትጠራለች
ይህ የሚናገረው ስለ ሞኝ ሲሆን ሰዎች እንዲመቱት የሚያደርግ ነገሮችን መናገሩ እርሱ ራሱ ሰዎቹ እንዲመቱት እንደጋበዛቸው ተደርጎ ተገልጿል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አፉ ሰዎች እንዲመቱት ያደርጋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
አፉ
እዚህ ላይ “አፍ” የሞኝ ሰው ንግግርን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተናገረው ንግግር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)