am_tn/pro/18/03.md

3.2 KiB

ንቀት ከእፍረትና ከስድብ ጋር አብረውት ይመጣሉ

እዚህ ላይ “ንቀት፣” “እፍረት፣” እና “ስድብ” ክፉ ሰውን የሚያጅቡት ሰዎች እንደሆኑ ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ሰዎች ለክፉ ሰው ንቀት ያሳያሉ ከዚህ የተነሳ እፍረትና ስድብ እንዲሰማው ያደርጋሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ስለ እርሱ ከእፍረትና ከስድብ ጋር ንቀት ይሰማቸዋል” ወይም 2) ክፉ ሰው ለሌሎች ንቀት ያሳያል ከዚህ የተነሳ እፍረትና ስድብ እንዲሰማቸው ያደርጋል” አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ለሌሎች ሰዎች ያለውን ንቀቱን ያሳያል ከዚህ የተነሳ እፍረትና ስድብ እንዲሰማቸው ያደርጋል” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እፍረትና ስድብ

እነዚህ ሁለት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ሁለቱም በአንድ ላይ ጥቅም ላይ የዋሉት ክፉው ሰው ወይም ደግሞ ሌሎች ሰዎች የተሰማቸውን “እፍረት” አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሃ ናቸው፤ የጥበብ ምንጭም የሚፈስ ወንዝ ነው

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ናቸው፣ በመጀመርያው መስመር ላይ ያለው ሰው ጥበበኛ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከጥበበኛ ሰው የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውኃ ናቸው፤ የጥበብ ምንጭም የሚፈስ ወንዝ ነው” (ትይዩነት እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሃ ናቸው

ይህ የሚናገረው የጥበበኛ ሰው ቃላት ጥልቅ እውቀት የሚገለጥባቸው እንደሆኑ ሲሆን በጣም ጥልቅና እንደ ጥልቅ ውኃ የጠለቁ እንደሆኑ ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት እንደ ጥልቅ ውኃ የጠለቁ ናቸው” ወይም “ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅና እውቀት ያለባቸው ናቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው አፍ

እዚህ ላይ ለተናገረው ነገር አጽንዖት ለመስጠት ሲባል ሰውየው በአፉ ተወክሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሰው” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

የጥበብ ምንጭም የሚፈስ ወንዝ ነው

ይህ የሚናገረው የጥበብ ምንጭ እንደሚፈልቅ ምንጭ የተትረፈረፈ እንደሆነ ነው፡፡ የምንጭ መፍለቅ እንደሚፈስ ወንዝ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የጥበብ ምንጭ ከሚፈልቅ ምንጭ እንደሚፈስ ውኃ የተትረፈረፈ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)