am_tn/pro/18/01.md

1.8 KiB

ራሱን ይለያል

“ከሌሎች ሰዎች ራሱን ይለያል”

ትክክለኛውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል

ይህ ትክክለኛውን ፍርድ ስለሚቃወም ሰው የሚናገር ሲሆን “ትክክለኛ ፍርድ” ከእርሱ ጋር እንደሚዋጋ ሰው ተደርጎ ተገልጿል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ከትክክለኛ ፍርድ ሁሉ ጋር አይስማማም” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ትክክለኛውን ፍርድ

“መልካም ፍርድ” ወይም “ጥበብ የተሞላበት ምርጫ”

ሞኝ ሰው በማስተዋል ደስታን አያገኝም፣ … እንጂ

“ሞኝ ሰው ስለ ማስተዋል ፈጽሞ አይገደውም፣ ነገር ግን ስለ … እንጂ” ይህ ሞኝ “ማስተዋልን” የደስታ ተቃራኒ እንደሆነ ያስባል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሞኝ ማስተዋል ይጠላል እናም ደስታን ብቻ ይፈልጋል” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

በራሱ ልብ ውስጥ ያለውን ነገር በመግለጥ እንጂ

ይህ ማለት ሞኝ ሰው ደስታ የሚያገኘው ለሌሎች ሰዎች በልቡ ምን እንደሚሰማውና ምን እንደሚመኝ በመንገር ብቻ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን ለሌሎች በልቡ ውስጥ ያለውን በመናገር ብቻ ነው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በልቡ ውሰጥ ያለውን

በሰው ልብ ውስጥ ያለው ነገር የሰውየውን ሃሳብና ስሜት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚያስበውን” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)