am_tn/pro/17/27.md

1.1 KiB

ጥቂት ቃላትን ይናገራል

ይህ የሚናገርበትን መንገድ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጥቂት ቃላት ይናገራል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሞኝ እንኳ እንደ ጥበበኛ ይቆጠራል

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ሞኝ እንኳ ጥበበኛ እንደሆነ ያስባሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

አፉንም ዘግቶ ዝም ሲል

ይህ አይናገርም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አይናገርም” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ምሁር እንደሆነ ይታሰባል

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ምሁር እንደሆነ ያስቡታል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)