1.6 KiB
1.6 KiB
ሞኝ ልጅ ለአባቱ ሐዘን ነው
ይህ ለአባቱ የሐዘን ምክንያት ስለሆነ ልጅ የሚናገር ሲሆን ልጁ ራሱ “ሐዘን” እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሞኝ ልጅ ለአባቱ ሐዘን ያመጣል”
ሞኝ ልጅ … ለወለደችውም እናቱ ምሬትን ያመጣል
ይህ ለእናቱ የምሬት ምክንያት ስለሆነ ልጅ የሚናገር ሲሆን ልጁ ራሱ “ምሬት” እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሞኝ ልጅ … ለእናቱ ምሬትን ያመጣል”
ለወለደችው
“እርሱን ለወለደችው”
ምሬት
ስሜታዊ ጉዳት፣ ሐዘን
በፍጹም መልካም አይደለም … መልካምም አይደለም
እነዚህ ሃሳቦች በአዎንታዊ መንገድ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህ ሁልጊዜ ስህተት ነው …. ይህ ሁልጊዜም ክፉ ነው” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)
ጻድቅ ሰው
የዚህ ሌላኛው ተቀበይነት ያለው ትርጉም የሚከተለው ነው፡- “ንጹህ ሰው” ባልሰራው ወንጀል ሌሎች እንደፈጸመ አድርገው የሚወነጅሉት ማንኛውም ሰው ነው፡፡
መግረፍ
በአሰቃቂ ሁኔታ መምታት
በሐቀኝት የሚሄድ
“ሐቀኝነት” የሚለው ቃል “ታማኝ” በሚለው ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ታማኝ የሆኑ” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)