am_tn/pro/17/13.md

1.2 KiB

ክፋት ከቤቱ ፈጽሞ አይርቅም

እዚህ ላይ “ክፉ” የሰውየውን ቤት የማይለቅ ሰው እንደሆነ ተደርጎ ተገልቷል፡፡ “ቤት” የሚለው ቃል በቁሙ መኖርያ በሚለው ሊተረጎም ይችላል ነገር ግን ለቤተሰቡም ምትክ ስም ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእርሱና በቤተሰቡ ላይ መጥፎ ነገሮች መፈጸም ይቀጥላል” ወይም “መጥፎ ነገሮች በእርሱና በቤተሰቡ ላይ ከመፈጸም በፍጹም አይከለከልም” (ሰውኛ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የጠብ መጀመርያ በሁሉም ስፍራ ውኃ እንደሚለቅ ሰው ነው

ይህ ጠብ በቀላሉ እንዴት እንደሚሰራጭ እና የፈሰሰ ውኃ በሁሉም ስፍራ እንዴት እንደሚፈስ ያነጻጽራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠብ መጀመር ውኃን እንደ መልቀቅና በሁሉም ስፍራ እንዲፈስ እንደማድረግ ነው” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይበረታል

“ይጀምራል” ወይም “ይነሳል”