am_tn/pro/17/03.md

2.3 KiB

ማቅለጫ ለብር ነው እቶንም ለወርቅ ነው

ይህ ወርቅና ብር እንዴት እንደሚነጥሩ የሚያሳይ ነው፡፡ ብረት መቅለጥ እንዲችልና በውስጡ ያለው ቆሻሻ እንዲወገድ የሚነጥረው እጅግ በጣም ሀይለኛ በሆነ የሙቀት ሃይል በማሞቅ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማቅለጫ ብር ለማንጠር ይጠቅማል፣ እቶን ደግሞ ወርቅ ለማንጠር ይጠቅማል” ፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ማቅለጫ

በጣም ከፍተኛ በሆነ ሙቀት ብረት የሚቀልጥበት ማሰሮ ነው፡፡

እግዚአብሔር ልብን ያነጥራል

ይህ የሰዎች ልብ ብረት እንደሆነ ያህል እነርሱ ክፉ እና ሞኝ መሆንን እንዲያቆሙ በሕይወታቸው ያለውን ማንኛውንም ቆሻሻ ለማስወገድ ሲል እግዚአብሔር ሰዎችን በማንጠር እንደሚፈትናቸው አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የሰዎችን ልብ ይፈትናል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉ ከንፈሮች

እዚህ ላይ “ከንፈሮች” የሚለው ቃል በሚከተሉት መንገድ ሊተረጎም ይችላል፡- 1) ለሰው ተዛምዶአዊ ነው ወይም 2) ከእነዚህ ከንፈሮች ለሚወጡት ቃላት ደግሞ ምትክ ስም ነው አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰው” ወይም “ክፉ ንግግር” (ተዛምዶአዊ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ጆሮውን ይሰጣል

ይህ ፈሊጥ ሲሆን “ማዳመጥ” የሚል ትርጉም አለው፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥፋት የሚያደርስ ምላስ

“ምላስ” የሚለው ቃል እንደሚከተለው ሊተረጎም ይችላል፡- 1) ለሰውየው ተዛምዶአዊ ዘይቤ ነው ወይም 2) ምላሱ ለሚፈጥረው ቃላት ደግሞ ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አጥፊ ሰው” ወይም “አጥፊ ንግግር” (ተዛምዶአዊ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)