የእግዚአብሔር ፍርሃት ጥበብን ያስተምራል
“ፍርሃት” እና “ጥበብ” የሚሉት ቃላቶች በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው እግዚአብሔርን ሲፈራ ጥበበኛ መሆንን ይማራል” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔርን መፍራት
ይህንን በምሳሌ 1:7 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡
ትህትና ከክብር በፊት ትመጣለች
አንድ ሰው እግዚአብሔር እርሱን ከማክበሩ በፊት ያ ሰው በመጀመርያ ትህትናን መማር አለበት ማለት ነው፡፡