am_tn/pro/15/29.md

1.6 KiB

እግዚአብሔር ከክፉ ሰዎች እጅግ ሩቅ ነው

ጸሀፊው ክፉ ሰዎች በአካል እግዚአብሔር ከእነርሱ እጅግ በጣም ሩቅ እንደሆነ ያህል እነርሱን እንደማይሰማቸው አድርጎ ይናራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ክፉ ሰዎችን አይሰማም” ወይም “እግዚአብሔር ለክፉ ሰዎች መልስ አይሰጥም“ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የዓይን ብርሃን

ጸሀፊው በአንድ ሰው ፊት የሚታየውን ደስታ ሲገልጽ የሰውየው ዓይኖች ብርሃን እንደሚፈነጥቁ አድርጎ ተናግሮታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ደስ የሚያሰኝ መግለጫ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለልብ ደስታን ያመጣል

“ልብ” የሚለው ቃል ሰውየውን ይወክላል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ፍልቅልቅ ፊት ያለው ሰው ደስተኛ ይሆናል ወይም 2) ፍልቅልቅ ፊት ያለው ሰው ሲመለከቱ ሌሎች ሰዎች ደስተኛ ይሆናሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰውን ደስተኛ እንዲሆን ያደርጋል” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

መልካም ወሬ ለሰውነት ጤና ነው

እዚህ ላይ “ሰውነት” የሚለው ቃል ሰውየውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መልካም ወሬ መስማት ሰውን ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ያደርጋል” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)