am_tn/pro/15/27.md

1.5 KiB

ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ልብ መልስ ከመስጠቱ በፊት አጥብቆ ያስባል

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል ለአእምሮ እና ለሃሳብ ምትክ ስም ነው፡፡ ይህ የሚያስብን ሰው ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጽድቅን የሚያደርግ ሰው መልስ ከመስጠቱ በፊት ምን መናገር እንዳለበት አጥብቆ ያስባል” (ምትክ ስም እና ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

የክፉ ሰዎች አፍ ክፋትን ሁሉ ያጎርፋል

ጸሐፊው ስለ ክፉ ሰዎች አፍ ሲናገር አፋቸው የፈሳሽ መያዣ ዕቃ እንደሆነና፣ ስለ ክፋት ሲናገር ደግሞ እነርሱን የሞላቸው ፈሳሽ እንደሆነ አድርጎ ተናግሮታል፡፡ “አፍ” የሚለው ቃል የሚናገሩትን ሰዎች የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎች ሁልጊዜ ክፉ ነገሮችን ይናገራሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

የክፉ ሰዎች አፍ ክፋትን ሁሉ ያጎርፋል

በአንተ ቋንቋ እነዚህን ቃላቶች ሁሉ በነጠላ ቁጥር ወይም በብዙ ቁጥር መተርጎም የበለጠ የተለመደ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የክፉ ሰው አፍ ክፋቱን ሁሉ ያጎርፋል” ወይም “የክፉ ሰዎች አፎች ክፋታቸውን ሁሉ ያጎርፋሉ”