am_tn/pro/15/19.md

1.4 KiB

የታካች ሰው መንገድ … የቅን ሰው መንገድ

ጸሐፊው ስለ ሰው ሕይወት ሲናገር ሰውየው የሚጓዝበት መንገድ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የታካች ሰው ሕይወት … የቅን ሰው ሕይወት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የታካች ሰው መንገድ በእሾህ እንደ ታጠረ ስፍራ ነው

ጸሐፊው የታካች ሰው የሕይወት ዘይቤን በእሾህ በታጠረ ስፍራ ለመራመድ ከመሞከር ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ ሁሉም ቢሆኑ ሰውየው እንዲሰቃይ ያደርጋሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የታካች ሰው ሕይወት በእሾህ በታጠረ ስፍራ ለመራመድ እንደሚሞክር ሰው ነው” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የቅን መንገድ ግን በሚገባ የተገነባ አውራ ጎዳና ነው

ጸሐፊው ቅን ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው የሚለማመዱትን በረከት በተደላደለ መንገድ እንደሚራመዱ አድርጎ ገልጾታል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በሚገባ የተገነባ አውራ ጎዳና

ይህ በጣም ሰፊ፣ ለጥ ያለ እና ምንም እንቅፋት ወይም የተቦረቦረ ነገር የሌለው መንገድ ነው፡፡