am_tn/pro/15/17.md

2.0 KiB

የአትክልት ምግብ

አትክልት በጣም ትንሽ ምግብ ያለበትን ትንሽ ማዕድ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትንሽ ማዕድ” ወይም “በጣም ትንሽ ምግብ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ፍቅር ባለበት

“ፍቅር” የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች እርስ በርሳቸው በሚዋደዱበት” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ጥላቻ ባለበት የሰባ ጥጃ ከመብላት

ይህ በገቢር ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው በጥላቻ ከሚያቀርበው የሰባ ጥጃ ይልቅ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰባ ጥጃ

ይህ የሚያመለክተው በሚገባ እንዲወፍር በጣም ብዙ ምግብ የተመገበ ጥጃን ይወክላል፡፡ ይ የሚወክለው በጣም ጣፋጭ ምግብ ወይም ድግስ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መንደላቀቅ ያለበት መዐድ” ወይም “ድግስ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ከጥላቻ ጋር

“ጥላቻ” የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች እርስ በርሳቸው በሚጣሉበት” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ጭቅጭቅን ያነሳሳል

ሰዎች የበለጠ እንዲጨቃጨቁ ማድረግ ጭቅጭቅን ማባባስ ወይም መቀስቀስ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ “ጭቅጭቅ” የሚለው ረቂቅ ስም “ተጨቃጨቀ” ተብሎ ሊገለጽ ይችላ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች የበለጠ እንዲጨቃጨቁ ማድረግ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)