am_tn/pro/15/13.md

1.5 KiB

ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል

እዚህ ላይ “ልብ” የሚወክለው ሰውየውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው ደስተኛ ሲሆን ፊቱ ይፈካል” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

መንፈስን ይሰብራል

ጸሐፊው ልቡ ስለተሰበረ ሰው ሲናገር የዚያ ሰው መንፈስ እንደተሰበረ ዕቃ አድርጎ ገልጾታል፡፡ ይህንን በምሳሌ 15:4 እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰውን ልቡ እንዲሰበር ያደርጋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የአስተዋይ ልብ

እዚህ ላይ “ልብ” የሚወክለው አእምሮንና ሃሳብን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የአስተዋይ ሰው አእምሮ” ወይም “አስተዋይ ሰው” (ምትክ ስም እና ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ይመገባል

እዚህ ላይ “አፍ” የሚወክለው ሰውየውን ነው፡፡ ጸሐፊው ሞኝ ነገሮች ስለሚፈልጉ ሞኞች ሲናገር ሞኝነትን እንደተመገቡ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሞኞች ሰዎች የሚመገቡት ምግብ እንደሆነ ዓይነት ሞኝነትን ይፈልጋሉ” (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)