am_tn/pro/15/11.md

2.2 KiB

ሲኦልና ጥፋት በእግዚአብሔር ፊት የታወቁ ናቸው

“ሲኦልና ጥፋት” የሚሉት ቃላቶች ሁሉም የሚያመለክቱት የሙታንን መኖርያ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ ሙታን መኖርያ ሁሉን ነገር ማወቁ በእግዚአብሔር ፊት የተገለጠ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ሙታን ስለሚኖሩበት ስፍራ ሁሉን ነገር ያውቃል” (ጥምር ቃል እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይልቁንም የሰው ልጆች ልብማ ምንኛ የተገለጠ ይሆን?

ይህ መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ እግዚአብሔር ስለ ሙታን መኖርያ ሁሉን ነገር ስለሚያውቅ፣ ስለ ሰዎች ልብ ሁሉን ነገር እንደሚያውቅ የበለጠ ግልጽ እንደሆነ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለዚህ የሰው ልጆችን ልብ በእርግጠኝነት ያውቃል!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጆች ልብ

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል ሃሳብንና ተነሳስቶትን ይወክላል፡፡ “የሰው ልጆች” የሚለው ሀረግ ለሰው ዘር ሁሉ የቆመ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሰዎች ሃሳብ” (ምትክ ስም እና ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ፌዘኛ ሰው እርምትን አይወድድም

“እርምት” የሚለው ቃል በግስ ቅርጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ፌዘኛ ሰው ሌሎች ሲያርሙት ይጠላል” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ጠቢባንም አይሄድም።

የእነርሱን ምሪትና ምክር ለመፈለግ ወደ ጠቢባን እንደማይሄድ የሚያመላክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምክራቸውን ለመፈለግ ወደ ጠቢባን አይሄድም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)