am_tn/pro/15/09.md

1.4 KiB

እግዚአብሔር የኃጢአተኞችን መንገድ ይጠላል

የኃጢአተኞች የሕይወት ዘይቤ እነዚህ ሰዎች እንደሚሄዱባቸው መንገዶች እንደሆኑ ተደርገው ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ኃጢአተኞች የሚኖሩትን የሕይወት ዘይቤ ይጠላል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጽድቅን የሚከታተለውን

ጽድቅን ለመኖር መትጋ ትክክለኛ ነገሮችን እንደመከታተል ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- በጽድቅ ለመኖር ጥረት የሚያደርግ ሰው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መንገድን የሚተው ሰው

እዚህ ላይ “መንገድን” የሚለው የጽድቅ መንገድን ያመለክታል፡፡ ጽድቅን ማድረግ የተወ ሰው በትክክለኛው መንገድ መሄድን እንዳቆመ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጽድቅን መኖር የተወ ሰው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርምትን የሚጠላ

“እርምት” የሚለው ቃል እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሌሎች ሲያርሙት የሚጠላ ሰው” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)