1.3 KiB
1.3 KiB
የጠቢባን ከንፈር እውቀትን ትዘራለች
“ከንፈር” የሚለው ጠቢባን የሚናገሩትን ይወክላል፡፡ ጸሐፊው ስለ እውቀት ጠቢባን ሲናገሩ በየአካባቢው የሚዘሩት ዘር እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የጠቢባን ንግግር እውቀትን ያሰራጫል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
የሞኞች ልብ ግን እንዲህ አይደለም
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ልብ” የሚለው ቃል ለሞኞች ተዛምዶአዊ ዘይቤ ሲሆን ትርጉሙም እንደ ጠቢባን እውቀትን አይዘሩም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሞኞች እውቀትን አይዘሩም” ወይም 2) ሞኞች በልባቸው ውስጥ እውቀት የላቸውም፣ እዚህ ላይ “ልብ” ለሃሳብ ተዛምዶአዊ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሞኞች እውቀትን አይረዱም” (ተዛምዶአዊ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
ቅን ሰዎች
“በጽድቅ የሚኖሩ ሰዎች”
በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው
“ያስደስተዋል”