am_tn/pro/15/03.md

1.8 KiB

የእግዚአብሔር ዓይኖች በሁሉ ስፍራ ናቸው

እዚህ ላይ “ዓይኖች” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ይወክላል ደግሞም የእርሱን ሁሉን ነገር የማየት ችሎታውን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ይመለከታል” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉዎችንና ደጎችን

“ክፉ” እና “ደግ” የሚሉት ቃላት ሰዎችን ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎችና መልካም ሰዎች” (የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)

ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው

“ምላስ” የሚለው ቃል ንግግርን ያመለክታል፡፡ ጸሐፊው ሌሎችን የሚያግዝና የሚያበረታታ ንግግር ስለተናገረው ሰው ሲናገር ንግግሮቹ ሕይወት የሚሰጥ ምግብ እንሚያቀርብ ዛፍ እንደሆኑ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መልካም ቃላቶች ሕይወት እንደሚሰጥ ዛፍ ናቸው (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጠማማ ምላስ ግን መንፈስን ይሰብራል

“ጠማማ ምላስ” የሚለው አታላይነት የተሞላና ጉዳት የሚያስከትል ንግግርን ያመለክታል፡፡ ጸሀፊው የተጎዳውን ወይም ተስፋ የቆረጠውን ሰው መንፈስ ቃላት እንደሰበሩት ዕቃ አድርጎ አቅርቦታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አታላይነት የተሞላ ንግግር ሰውን ተስፋ እንዲቆርጥ ያደርገዋል” (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)