am_tn/pro/15/01.md

1.9 KiB

የለዘበ መልስ ቁጣን ይመልሳል

አንድ ሰው ቁጣውን እንዲያቆም ማድረግ የዚያን ሰው ቁጣ መመለስ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለአንድ ሰው በጨዋነት መልስ መስጠት የዚያን ሰው ቁጣ ያበርዳል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መጥፎ ቃል ግን ቁጣን ያስነሳል

አንድ ሰው የበለጠ እንዲቆጣ ማድረግ ቁጣን ማነሳሳት ወይም ማቀጣጠል ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን መጥፎ ቃል መናገር ያንን ሰው የበለጠ እንዲቆጣ ያደርገዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የጥበበኛ ሰዎች ምላስ እውቀትን ያሳምራል

እዚህ ላይ “ምላስ” የሚለው ቃል የሚናገረውን ሰው የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበበኛ ሰዎች ሲናገሩ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

እውቀትን ያሳምራል

“እውቀትን ማራኪ ያደርጉታል” ወይም “እውቀትን በትክክል ይጠቀማሉ”

የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ያፈልቃል

ጸሐፊው የሞኞችን አፍ የፈሳሽ መያዣ ዕቃ እንደሆነ፣ ሞኝነት ደግሞ እነርሱን የሞላቸው ፈሳሽ እንደሆነ አድርጎ ተናግሮታል፡፡ ሞኞች ሲናገሩ አፋቸው ፈሳሹን ያፈሳል፡፡ “አፍ” የሚለው ቃል የሚናገሩትን ሰዎች የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሞኞች ሁልጊዜ ሞኝነትን ይናገራሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)