am_tn/pro/12/25.md

975 B

ጭንቀት

በጣም ከባድ የፍርሃት ወይም ስጋት፣ ትካዜ ስሜት

ያዋርደዋል

“ማዋረድ” አንድ ሰው በነጻነት እንደሚገባ እንዳይንቀሳቀስ ለማድረግ በጣም ከባድ ሸክም በሰውየው ላይ የመጫን ሃሳብን ይወክላል፡፡ ይህ ሀረግ አንድን ሰው እንዲያዝን ወይም እንዲጨነቅ ማድረግ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዲያዝን ወይም እንዲጨነቅ ማድረግ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል

“ቃል” የሚለው ረቂቅ ስም “ተናገረ” በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን ሌሎች ለእርሱ በደግነት ሲናገሩ እንደገና ደስተኛ ይሆናል” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)