am_tn/pro/12/07.md

1.5 KiB

ኀጥኣን ይገለበጣሉ

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ክፉ ሰዎችን ይገለብጣሉ” ወይም “ሰዎች ክፉ ሰዎችን ከስልጣናቸው ያስወግዱአቸዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ በዘይቤአዊ አነጋር ቅድመ አያቶችን፤ የትውል ሀረግን ወይም ሌሎች ዘመዶችን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቤተሰብ” ወይም “የትውልድ ሀረግ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ሰው በጥበቡ ብዛት ይመሰገናል

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ጥበብ ያላቸውነ ሰዎች ያወድሳሉ (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ጠማማ ምርጫዎች የሚያደርግ ግን ይናቃል

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ክፉ ሃሳብ ሁልጊዜ የሚያስብን ሰው ይጠላሉ” ወይም “ሰዎች መልካምን ነገር አጣምሞ በመጥፎ የሚለውጥን ሰው ይጠላሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)