1.5 KiB
1.5 KiB
ሰው በክፋት ላይ ተመስርቶ ጸንቶ ሊቆም አይችልም
ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ነገር በማድረግ ማንም ሰው ዋስትናና ጥበቃ ሊኖረው አይችልም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
አይነቀልም
“አይነቀልም” እንደ ተክል ወይም ዛፍ ከምድር መነቀልን ይወክላል፡፡ ጽድቅ የሚያደርጉ ሰዎች ላይ ይህ አይሆንም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥልቅ ስር እዳላቸው ተክሎች ጽኑ ናቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት
ዘውድ አንድ ሰው ሊቀበለው የሚችለውን ታላቅ ክብር ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መልካም ሴት ለባሏ የታላቅ ክብር ምልክት ናት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
አሳፋሪ ሴት ግን አጥንቱን እንደሚያበሰብስ በሽታ ናት
አጥንትን የሚያበሰብስ በሽታ የሰው ሕይወት መበለላሸትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚስት አሳፋሪ ተግባር የባሏን መልካም ተጽዕኖና ደስታ ያጠፋል” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)