943 B
943 B
ተግቶ የሚፈልግ ሰው
በጥንቃቄና በማያቋርጥ ጥረት የሚፈልግ ሰው
ይወድቃል
ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ “ይወድቃል” ጥፋትን እና ውድቀትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይጠፋል” ወይም “ለወደፊት ክፉ ነገር ይጠብቀዋል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)
ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ
“ቅጠል” እድገትንና ባለጠግነትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ጤነኛ ቅጠል እንደሚያድግ እንደዚሁ ይበለጽጋሉ” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ጽድቅን የሚያደርጉ ይለመልማሉ
ይህ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ያድጋሉ ወይም ይበለጽጋሉ ማለት ነው፡፡