1.0 KiB
1.0 KiB
ያለውን የሚበትን ሰው አለ፥ እርሱ የበለጠ ይሰበስባል
ይህ በቸርነት በመስጠት የበለጠ ባለጠጋ ለሆነ ሰው ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንዳንድ ሰዎች ለሌሎች በነጻ ይሰጣሉ፣ እንዲህም ሆኖ ግን የበለጠ ባለጠጋ ይሆናሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
የሚበትን
ይህ ሰው እህል እንዲበቅል ዘርን እንደሚበትን ግልጽ ማድረግ ያስፈልግሃል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ብዙ ዘር የሚበትን ሰው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ እና ተተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
የበለጠ ይሰበስባል
“የበለጠ ያገኛል”
መስጠት የሚገባውን ያለ ቅጥ የሚይዝ
ይህ ባለመስጠት ባለጠጋ መሆን እንደሚችል የሚያስብን ሰው ይወክላል፡፡