985 B
985 B
አጠቃላይ መረጃ፡-
በምዕራፍ 11 ውስጥ ያሉ ብዙ ቁጥሮች ትይዩነትን ያነጻጽራሉ፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ትክክለኛ ያልሆነ ሚዛን ይጠላል
“ሚዛን” በስምምነት የሚደረግ ትክክለኛ መለኪያን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር አታላይነት ያለበትን መለኪያ ይጠላል” ወይም “እግዚአብሔር ሰዎች አታላዮች ሲሆኑ ይጠላል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ትክክለኛ ሚዛን ግን ደስ ያሰኘዋል
“ትክክለኛ ሚዛን” በስምምነት የሚሆን ልክነትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን እርሱ በሀቀኛ መንገድ ይደሰታል” ወይም “ነገር ግን እርሱ ሰዎች ሀቀኛ ሲሆኑ ይደሰታል”