am_tn/pro/09/16.md

1.3 KiB

አላዋቂ ነው

“ልምድ የሌለው ወይም የአእምሮ ብስለት የሌለው ነው”

ወደዚህ ፈቀቅ ይበል

“ይህንን መንገድ ይተውና ወደዚህ ይምጣ”

እንዲህ አለች

ይህች በምሳሌ 9፡13 ላይ የተዋወቀችው ሞኝ ሴት ናት፡፡

እነዚህ አእምሮ የጎደላቸው

“እነዚህ ጥበብ የሌላቸው” ወይም “እነዚህ ጠቢባን ያልሆኑ”

የተሰረቀ ውኃ ጣፋጭ ነው፣ በምስጢር የበሉት እንጀራም ደስ ያሰኛል

ይህች ሞኝ ሴት ከእርስዋ ጋር ከተኙ ደስተኛ እንደሚሆኑ ለወንዶች ለመናገር ስለ ተሰረቀ ውኃ እና በምስጢር ስለተበላ እንጀራ አስደሳችነት ትናገራለች፡፡ ይህ በተነጻጻሪ ዘይቤ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡- “የሰረቅኸው ውኃ እና በምስጢር የበላኸው ደስ እንደሚያሰኝህ ሁሉ ከእኔ ጋር ብትተኛ በእኔ ደስ ትሰኛለህ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሙታን ከዚያ እንዳሉ

“ወደ እርስዋ የሄዱ ወንዶች አሁን ሞተዋል”

በሲኦል ጥልቀት

“ሲኦል” የሚያመለክተው የሙታን ዓለምን ነው፡፡