am_tn/pro/09/10.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እነዘህ ቁጥሮች የጥበብን መልእክት ይፈጽማሉ፡፡

የእግዚአብሔር ፍርሃት

ይህንን በምሳሌ 1፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡

ዘመንህ በእኔ ይበዛል

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ዘመንህን እኔ አበዛዋለሁ” ወይም “እኔ ብዙ ዘመን እንድትኖር አደርግሃለሁ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ

ጥበብ እንደ ሴት ተመስላ እዚህ መናገር ቀጥላች፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዘመንህ በእኔ ይበዛልና፥ የሕይወትህም ዕድሜ ይጨመርልሃል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ጥቅም ላይ የዋሉትም ጥበብ ያላትን ታላቅ ጥቅም አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

የሕይወትህም ዕድሜ ይጨመርልሃል

ጥበብ ስለ ሕይወት ዕድሜ ቁሳዊ ነገሮች እነደሆኑ አድርጋ ትናገራለች፡፡ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ለአንተ የሕይወት ዕድሜ እጨምርልሃለሁ” ወይም “ረጅም ዕድሜ እንድትኖር አደርግሃለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ጠቢብ ብትሆን … ፌዘኛም ብትሆን

እነዚህ ሁለት ሃሳቦች ሰዎች ከጥበባቸው የተነሳ ለራሳቸው ጥቅም እንደሚያገኙ ፌዘኞች ደግሞ ከባህርያቸው የተነሳ እንደሚሰቃዩ የሚናገሩ ይመስላሉ፡፡

ለብቻህ ትሸከመዋለህ

ይህ ከመጥፎ ባሕርዩ የተነሳ ሰው የሚመጣበትን መዘዝ አንድ ሰው በጀርባው ሊሸከመው የሚገባው ከባድ ሸክም እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)