am_tn/pro/09/03.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እነዚህ ቁጥሮች እንደ ሴት የቀረበችውን የጥበብን መልእክት ማቅረብ ይጀምራሉ፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰራተኞችዋን ላከች

እነዚህ ሰራተኞች ወደ ውጭ ሄደው ጥበብ ወዳዘጋጀችው ድግስ እንዲመጡ ሰዎችን ጋበዙአቸው፡፡

ሰራተኞችዋ

ጥበብን የመሰሉ የተከበሩ ሴቶችን የሚያገለግሉ ወጣት ሴቶች ወይም ልጃገረዶች፡፡

ጠራች

“እርስዋ አወጀች” ወይም “እርስዋ ጥሪ አደረገች” አማራጭ ትርጉም፡- “እርስዋ ደጋግማ በመጮህ ጥሪዋን አስተላፈች”

በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ

ግብዣው በሁሉም ሰዎች ዘንድ በሚገባ መደመጥ እንዲችል ከፍ ባለ ድምጽ የተላለፈው በከፍተኛ ስፍራ ላይ ነው፡፡

አላዋቂ የሆነ ማን ነው? … አእምሮ የጐደለውም ይምጣ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች የሚገልጹት በሕይወታቸው የበለጠ ጥበብ የሚያስፈልጋቸው ተመሳሳይ ዓይነት ሰዎችን ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ጥያቄው የቀረበው እንዲህ ለመሰሉ ለሁሉም ሰዎች ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- አላዋቂ የሆነ ማንኛውም ሰው፣ አእምሮ የጎደለውም ሁሉ ይምጣ”

አላዋቂ

“ልምድ የሌለው ወይም የአእምሮ ብስለት የሌለው”

ወደዚህ ፈቀቅ ይበል

“መንገዱን ይተውና ወደ ቤቴ ይምጣ”