am_tn/pro/09/01.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እነዚህ ጥቅሶች ጥበብ ለሰዎች መልካም ምክር የምትሰጥ ሴት ተደርጋ የተገለጸችበት ተምሳሌት ይጀምራሉ፡፡(ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥበብ ሠራች

ፀሐፊው ስለ ጥበብ የራስዋን ቤት እንደሰራች ሴት አድርጎ ያቀርባታል፡፡ ቤትዋን ሠራች

ፍሪዳዎቿን አረደች

ይህ ጥበብ እራት በምታቀርብበት ጊዜ ስጋቸው የሚበላውን እንስሳት የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለእራት የሚቀርበውን ስጋ ለማዘጋጀት ፍሪዳዎችን አረደች” (ምትክ ስም እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የወይን ጠጅዋን ደባለቀች

በጥንቷ እስራኤል ሰዎች ብዙ ጊዜ የወይን ጠጅን ከውኃ ጋር ይደባልቁ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የወይን ጠጇን ከውኃ ጋር በመደባለቅ አዘጋጀች” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ማዕድዋን አዘጋጀች

“እርስዋ ማዕድዋን አዘጋጀች”