am_tn/pro/08/32.md

1.5 KiB

አሁን

ይህ የልጆቹን ትኩረት ወደ ትምህርቱ መደምደሚያ እንዲያደርጉ ለማገዝ ነው፡፡

አድምጡኝ

አሁንም ጥበብ ስለራስዋ እየተናገረች ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መንገዴን የሚጠብቁ

እዚህ ላይ “መንገዴን” የሚወክለው የጥበብን ባሕርይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ የማስተምረውን የሚያደርጉ” ወይም “የእኔን ምሳሌ የሚከተሉ ሰዎች” (ተላዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቸል አትበል

“ግድየለሽ አትሁን” አማራጭ ትርጉም፡- “ትኩረት ለመስጠትህ እርግጠኛ ሁን” ወይም “ለመከተል እርግጠኛ ሁን” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ጥበብ ቤት እንዳላት ተገል ጧል፤ “መትጋት” ለሚለው ቃል ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉ፡- 1) ጥበበኛ ሰው እርስዋን ለማገልገል በማለዳ በጥበብ ቤት መግቢያ ሆኖ ይጠብቃል፣ ወይም 2) ጥበበኛ ሰው እርስዋ እንድትመጣና እንድታስተምረው በጥበብ ቤት መግቢያ ሆኖ ይጠብቃል፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)