am_tn/pro/08/28.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ጥበብ መናገርዋን ቀጥላለች፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ተመሰረተ

ወደ ቋሚ ማንነት ማምጣት

የቀላይን ምንጮች ባጸና ጊዜ

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ምንጮችን በቀላይ ውስጥ ባጸና ጊዜ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የቀላይ ምንጮች

የጥንት ዕብራውያን ውቅያኖስ ውኃውን የሚያገኘው ከባህር ጣጭኛው ክፍል ውስጥ ካሉት ምንጮች ነው ብለው ያስተምሩ ነበር፡፡

ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ

ለውቅያኖሶች ዳርቻ በፈጠረላቸው ጊዜ፡፡ “የባህር ዳርቻ” ውቅያኖሶችን ከደረቅ መሬት ይለያቸዋል፡፡

የምድርም መሰረት የት መሆን እንዳለበት በወሰነበት ጊዜ

“ምድር” የሚለው የዕብራይስጡ ቃል ብዙ ጊዜ “መሬት” የሚል ትርጉም አለው፡፡

የምድርም መሰረት የት መሆን እንዳለበት በወሰነበት ጊዜ

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ለምድር መሰረት ዳርቻ ባስቀመጠለት ጊዜ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)