am_tn/pro/08/06.md

1.2 KiB

ከንፈሮቼ ሲከፈቱ

እዚህ ላይ “ከንፈሮች “ የሚወክለው የሚናገርበትን የሰውን አንደበት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለመናገር አንደበቴን ስከፍት” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ቅን

ተገቢ የሆነ ወይም ፍትሃዊ

አፌ ይናገራል

እዚህ ላይ “አፍ” የሚወክለው የሚናገረውን ሰው ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናገራለሁ” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

እውነትን

“ሰዎች ሊያምኑት የሚችሉት”

ከንፈሮቼም ክፋትን ይጠላሉ

እዚህ ላይ “ከንፈሮች” የሚወክሉት የሚናገረውን ሰው ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፋትን እጠላለሁ” ወይም “ክፉ ነገሮችን መናገር በእኔ ዘንድ የተጠላ ነው” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፋት

እዚህ ላይ “ክፋት” የሚለው ረቂቅ ስም የሚወክለው ክፉ ንግግርን ነው፡፡ (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)