am_tn/pro/07/24.md

1.5 KiB

አሁን

ይህ በዚህ ትምህርት ማጠቃለያ ላይ የተናጋሪው ወንድ ልጆች ትኩረት ላይ ለማነጣጠር የተነገረ ነው፡፡

ልብህ ወደ መንገዶቿ አያዘንብል በጎዳናዋ አትሳት።

እዚህ ላይ “መንገዶች” ማለት ሰው ሊሄድበት የሚመርጠው መንገዶች ናቸው፡፡ ይህ የሰውን ባሕርይ ማለትም በሕይወቱ ሊፈጽማቸው የወሰናቸውን ነገሮች ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ልብህ ከአመንዝራይቱ ሴት መንገዶች በጣም ርቆ እንዲቆይ አድርግ” ወይም “አመንዝራይቱ ሴት የምታደርጋቸውን ነገሮች እንዲያደርግ ልብህ እንዲሻ አትፍቀድለት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ልብህ

እዚህ ላይ “ልብ” ሰውን ይወክላል፣ ለፍላጎቱም አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ”(ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

በመንገዶቿ አትሳት

ይህ ከቀደመው ዓረፍተ ነገር ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡ የመጀመርያውን ማስጠንቀቂያ የሚያጠናክር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእርስዋ መንገድ ለመሄድ ስትል ትክክለኛውን መንገድ አትተው” (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)