am_tn/pro/07/22.md

1.8 KiB

በድንገት ተከትሏት ሄደ

ወጣት ወንድ ምን ማድረግ እንዳለበት ለማሰብ የሚወስደው ጊዜ በጣም አጭር እንደሆነ ይህ ሃሳብ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርስዋን ተከትሎ ለመሄድ በፍጥነት ወሰነ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለመታረድ እንደሚነዳ በሬ

ይህ ወጣት ወንድ በአላዋቂነትና ሳይጠረጥር አመንዝራይቱን ተከትሎ የሄደበት መንገድ ሶስቱ እንስሳት የገቡበትን አደጋ ባለማወቅ ከሄዱበት መንገድ ጋር ተነጻጽሯል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መታረድ

ይህ ስጋውን ለመብላት እንስሳን ማረድ ያመለክታል፡፡

አጋዘን

ይህን ቃል በምሳሌ 5፡19 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡

ፍላጻ ጉበቱን እስኪወጋው ድረስ

ይህ ክፍል አዳኙ አጋዘኑን በወጥመድ የያዘው በፍላጻ ለመውጋት እንደሆነ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አዳኝ በጣም ዋነኛ የሆነውን የሰውነቱን ክፍል እስኪወጋው ድረስ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ጉበት

እዚህ ላይ ይህ ብልት የአጋዘኑን በጣም ዋነኛ የሰውነት ክፍል ይወክላል፡፡

ሕይወቱን ያሳጣዋል

ይህ ሰው ከዚህ የተነሳ ይሞታል ለማለት የአባባል ዜይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይገድለዋል” ወይም “ወዲያውኑ ይሞታል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)