am_tn/pro/07/19.md

1.5 KiB

በቤቱ የለም

“በቤት ውስጥ የለም”

ሙሉ ጨረቃ

ጨረቃ ሙሉ የምትባለው ሙሉ በሙሉ ክብ ቅርጽ ስትይዝና ከፍተኛ ብርሃንዋን ስታንጸባርቅ ነው፡፡

እንዲስት ታደርገዋለች

አንድ ሰው በሆነ መንገድ አንድ ነገር እንዲያደርግ ማነሳሳት በመንገድ ይሄድ የነበረ ሰው አቅጣጫውን እንደቀየረ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ገፋፋችው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርስዋ … እርስዋ … የእርሱ

ሴትዮዋ በትዳር ያለች ስትሆን ነገር ግን “ከእርሱ” ማለትም ከወጣት ወንድ ጋር መተኛት የምትፈልግ ሴት ናት፡፡

ለስላሳ ከንፈር

እዚህ ላይ “ከንፈር” የሚወክለው የሰውን ንግግር ነው፡፡ አንድ ሰው እውነተኛ ያልሆነ ነገር በመናገር ሌላውን ሰው ከፍ ከፍ ሲደርገው እነዚህ በልዝብነት የተነገሩ ቃላቶች እንደ ለስላሳ እቃዎች ተደርገው ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሽንገላ፣ የማታለያ ቃላት” (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲስት አደረገችው

“ክፉ ነገር እንዲሰራ አሳመነችው” አማራጭ ትርጉም፡- “ከእርስዋ ጋር ኃጢአት እንዲሰራ አሳመነችው”